am_amo_text_udb/07/01.txt

3 lines
913 B
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\c 7 \v 1 እግዚአብሔር አምላካች ሰብላችንን የሚያጠፉ አንበጦችን እንደሚልክ በራእይ ገለጠልኝ፤ ይህም የሚሆነው ልክ የንጉሡ የመከሩ ድርሻ ከተሰበሰበ በኋላና ቀሪው መከር ለመሰብሰብ ገና ዝግጁ ባልነበረበት ጊዜ ነበር፡፡
\v 2 በዚያ ራእይ እነዚያ አንበጦች ሲመጡና ለምለም የሆነውን ማንኛውንም ነገር ሲበሉ ተመለከትሁ፤ ከዚያ በኋላም፣ ‹‹እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፣፣ እባክህን ይቅር በለን! እኛ የእስራኤል ሕዝቦች እጅግ ምስኪኖች ነን፣ ልንቋቋመው እንዴት እንችላለን? ብዬ አለቀስሁ፡፡
\v 3 ስለዚህ እግዚአብሔር ዐሳቡን ለውጦ፣ ‹‹ይህ አይፈጸምም›› አለ፡፡