am_amo_text_udb/04/08.txt

2 lines
849 B
Plaintext

\v 8 ሰዎቻችሁ ውሃ ለማግኘት ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ በመሄድ ይዘለፈለፋሉ፤ ሆኖም የሚጠጣ በቂ ውሃ እንኳን አያገኙም፤ እንደዚያ ቢሆንም እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፡፡ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬዋለሁና ይህ በእርግጥ ይሆናል!
\v 9 የእህል እርሻዎቻችሁ እንዲደርቁ፣ የአትክልት ስፍራዎቻችሁና የወይን ተክሎቻችሁ በዋግ እንዲመቱ አደረግሁ፤ በበለስና በወይራ ዛፎቻችሁ ያሉትን ቅጠሎች የሚበሉ አንበጣዎችን ላክሁ፤ ይህንን ባደርግም እናንተ ግን ተዋችሁኝ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬዋለሁና ይህ በእርግጥ ይፈጸማል!