am_amo_text_udb/03/11.txt

2 lines
696 B
Plaintext

\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችን ጠላቶቻቸው ፈጥነው ይመጣሉ፣ መከላከያዎቻቸውን አፍርሰው እነዚያን ውድ ነገሮች ይወስዳሉ ይላል፡፡
\v 12 እግዚአብሔር እንደዚህ ብሏል፡- ‹‹አንበሳ በጎችን ሲያጠቃ እረኛ አንዳንድ ጊዜ ከአንበሳው አፍ የበጉን ሁለት እግሮች ወይም አንዱን ጆሮ ብቻ ማስጣል ይችላል፤ ከሰማርያም በተመሳሳይ ሁኔታ ጥቂት ሰዎች ብቻ ያመልጣሉ፤ እነርሱም የወንበር ስባሪና ከአልጋው ከፊሉን ብቻ ማስቀረት ይችላሉ››