\c 3 \v 1 እናንተ የእስራኤል ሕዝቦች ሆይ፣ አባቶቻችሁን ሁሉ ከግብፅ አወጣኋቸው፤ ስለዚህ ስለ እናንተ የምናገረውን አድምጡ፡፡
\v 2 በምድር ላይ ካሉ የሕዝብ ወገኖች ሁሉ፣ እናንተን ብቻ መረጥሁ ተንከባከብኋችሁም፡፡ ስላደረጋችኋቸው ኃጢአቶች የምቀጣችሁ ከዚህ የተነሣ ነው፡፡››