\c 2 \v 1 ደግሞ እግዚአብሔር እንደዚህ አለ፡- ‹‹ስላደረጓቸው ብዙ ኃጢአቶች የሞዓብን ሕዝብ እቀጣለሁ፤ ዐመዳቸው እንደ ኖራ ነጭ እስከሚሆን ድረስ የኤዶምያስን ንጉሥ አጥንቶች ቈፍረው ካወጡ በኋላ ሙሉ በሙሉ አቃጥለዋቸዋልና እነርሱን ለመቅጣት የወሰንሁትን ውሳኔ አልለውጥም፡፡