am_amo_text_udb/01/11.txt

1 line
874 B
Plaintext

\v 11 ደግሞም እግዚአብሔር እንደዚህ አለኝ፡- ‹‹ሕዝቦቻቸው ስላደረጓቸው ብዙ ኃጢአቶች የኤዶምያስን ሕዝብ እቀጣለሁ፣ የዔሳው ወንድም የያዕቆብ ዝርያ የሆኑትን የእስራኤል ሕዝብ በፍጹም ሳይራሩላቸው ስላሳደዷቸውና በሰይፍ ስለገደሏቸው እነርሱን ለመቅጣት የወሰንሁትን ውሳኔ አልለውጥም፡፡ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ከመጠን በላይ ተቈጥተውባቸው ነበር፤ በእነርሱ ላይ መቈጣታቸውንም ቀጥለዋል፡፡ \v 12 በኤዶምያስ ባለው የቴማን አውራጃ ላይ እሳት እንዲነድ አደርጋለሁ፤ የኤዶምያስ ታላቂቱ ከተማ ባሰራ ምሽጎችንም ሙሉ በሙሉ አቃጥላለሁ፡፡››