am_amo_text_udb/01/01.txt

2 lines
1.1 KiB
Plaintext

\c 1 \v 1 ይህ መልእክት ከኢየሩሳሌም በስተደበቡ በቴቁሔ ከተማ አቅራቢያ ለነበረው እረኛ ለአሞጽ እግዚአብሔር የሰጠው ነው፡፡ እርሱ እስራኤልን የሚመለከተውን ይህንን መልእክት በራእይ ከታላቁ የምድር መናወጥ ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ ተቀበለ፡፡ ይህም የሆነው ኦዝያን የይሁዳ ንጉሥ፣ የንጉሥ ዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም ደግሞ የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ወቅት ነበር፡፡
\v 2 አሞጽ እንደዚህ ነበር ያለው፡- ‹‹በኢዮሩሳሌም ካለው ከጽዮን በሚናገርበት ጊዜ እግዚአብሔር ከፍ ባለ ድምፅ ይጮኻል፤ ድምፁም እንደ ነጐድጓድ ድምፅ ይሆናል፡፡ ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ፣ እናንተ እኞረች በጎቻችሁን የምታሰማሩባቸው የግጦሽ ቦታዎች ይደርቃሉ፤ በቀርሜሎስ ተራራ ጫፍ ያለውም ሣር ይጠወልጋል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ዝናቡ እንዳይዘንብ ያዛል››