\c 6 \v 1 በእነዚህ ወራት፣ የደቀ መዛሙርት ቊጥር እየበዛ በሄደ ጊዜ፣ ከግሪክ የመጡት አይሁድ በዕብራውያን ላይ ማጕረምረም ጀመሩ፤ ምክንያቱም መበለቶቻቸው በየዕለቱ የምግብ ዕደላ ላይ ቸል ተብለውባቸው ነበር።