am_act_text_ulb/13/46.txt

3 lines
641 B
Plaintext

\v 46 ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት ተናገሩ፤ እንዲህም አሉ፤ “የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። ቃሉን ከራሳችሁ ስትገፉትና ለዘላለም ሕይወት የተገባችሁ እንዳልሆናችሁ ራሳችሁን ስትቈጥሩ ዐይተናችሁ፣ ወደ አሕዛብ ዘወር የምንል መሆናችንን ተመልከቱ።
\v 47 ጌታ፣ ‘እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለድነት ትሆን ዘንድ፣
ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’” በማለት አዞናልና።