am_act_text_ulb/25/06.txt

1 line
668 B
Plaintext

\v 6 ፊስጦስም ስምንት ወይም ዐሥር ተጨማሪ ቀናት ከቆየ በኋላ፣ ወደ ቂሣርያ ወረደ። በማግስቱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ። \v 7 ጳውሎስም በደረሰ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ በአጠገቡ ቆሙ፤ በማስረጃ ማረጋገጥ ያልቻሉትንም ብዙ ከባድ ክስ አቀረቡ። \v 8 ጳውሎስ፣ “የአይሁድን ስም ቢሆን፣ ቤተ መቅደስን ቢሆን፣ ቄሣርንም ቢሆን በደል አልፈጸምሁም” ብሎ ራሱን ተከላከለ።