am_act_text_ulb/23/22.txt

1 line
746 B
Plaintext

\v 22 ስለዚህ ሻለቃው ወጣቱን ልጅ፣ “ስለ እነዚህ ነገሮች ለእኔ መግለጥህን ለማንም እንዳትናገር” ብሎ ካስጠነቀቀው በኋላ አሰናበተው። \v 23 ከመቶ አለቆቹም ሁለቱን ወደራሱ ጠርቶ፣ “እስከ ቆጣርያ ለመሄድ ዝግጁ የሆኑ ሁለት መቶ ወታደሮችን፣ ሰባ ፈረሰኞችንና ሁለት መቶ ባለ ጦሮችን አዘጋጁ፤ ከሌሊቱም በሦስተኛው ሰዓት ትንቀሳቀሳላችሁ” አላቸው። \v 24 ጳውሎስ ወደ ሀገረ ገዢ፣ ወደ ፊልክስ የሚሄድበትንም ከብት እንዲያዘጋጁና በሰላም እንዲያደርሱት አዘዛቸው።