\c 10 \v 1 በቂሣርያ ከተማ ውስጥ የኢጣሊቄ ክፍለ ሰራዊት በሚባል የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ሰው ነበረ። \v 2 እርሱም መንፈሳዊ፣ ከቤተሰቡ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ ለአይሁድ ብዙ ገንዘብ የሚሰጥና ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር የሚጸልይ ሰው ነበረ።