am_act_text_ulb/08/09.txt

1 line
598 B
Plaintext

\v 9 ነገር ግን በዚያች ከተማ ውስጥ ቀደም ሲል የጥንቆላ ሥራ ይሠራ የነበረ ሲሞን የሚባል ሰው ነበረ፣ ተፈላጊ ሰው እንደ ሆነ እየተናገረ የሰማርያን ሰዎች ያስደንቅ ነበር። \v 10 ሳምራውያን በሙሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ “ይህ ሰው ታላቅ የሚባለው የእግዚአብሔር ኀይል ነው” እያሉ በሚገባ ያደምጡት ነበር። \v 11 በጥንቆላ ሥራው ለረጅም ጊዜ ያስገርማቸው ስለ ነበር አደመጡት።