am_act_text_ulb/25/13.txt

1 line
966 B
Plaintext

\v 13 ከጥቂት ቀናትም በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ይፋዊ የሥር ጉብኝት ለማድረግ ሊጎበኙት ወደ ቂሣርያ ወደ ፊስጦስ ሄዱ። \v 14 ንጉሥ አግሪጳ በዚያ ብዙ ቀናት ከተቀመጠ በኋላ፣ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ አቀረበ፤ እንግዲህም አለ፤ “ፊልክ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ። \v 15 እኔ በኢየሩሳሌም በነበርሁ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ክስ መሥርተውበት ለእኔ አመለከቱ፤ እንድፈርድበትም ለመኑኝ። \v 16 ለዚህም የተከሰሰው ሰው በከሳሾቹ ፊት ቀርቦ ለተከሰሰበት ነገር እንዲከላከል ዕድል ሳይሰጠው አንድን ሰው አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ አይደለም ብዬ መልስ ሰጠሁ።”