am_act_text_ulb/23/06.txt

1 line
831 B
Plaintext

\v 6 ጳውሎስም የሸንጎው አባላት ከፊላቸው ሰዱቃውያን፣ ሌሎቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን ሲያይ፣ በሸንጎ መካከል ሆኖ በከፍተኛ ድምጽ፣ “ወንድሞች ሆይ፤ እኔ የፈሪሳዊ ልጅ የሆንሁ፣ ፈሪሳዊ ነኝ። ፍርድ ፊት የቀረብሁትም የሙታን ትንሣኤ እንዳለ ስለማንም ነው” አላቸው። \v 7 ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ክርክር ተነሣ፤ ጉባኤውም ተከፋፈለ። \v 8 ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም፤ መላእክትም የሉም፤ መናፍስትም የሉም ስለሚሉና፣ ፈሪሳውያን ግን እነአዚህ ሁሉ አሉ ስለሚሉ ነው።