am_act_text_ulb/21/34.txt

1 line
644 B
Plaintext

\v 34 ከሕዝቡም ግማሾቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ ግማሹ ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይንጫጩ ነበር። ሻለቃውም ከጫጫታው ሁሉ የተነሣ፣ ስለ ምን እንደሚጮኹ እንኳ መለየት አልቻለም፤ ስለዚህ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ምሽግ እንዲያገቡት አዘዘ። \v 35 ጳውሎስ ወደ መወጣጫው ደረጃ በደረሰ ጊዜ፣ ከሕዝቡ ረብሻ የተነሣ፣ ወታደሮቹ ተሸክመውት ሄዱ። \v 36 ሕዝቡም፣ “አስወግደው!” እያሉ ከኋላ እየተከተሉት ይጮኹ ነበር።