am_act_text_ulb/11/04.txt

1 line
591 B
Plaintext

\v 4 ጴጥሮስ ግን እንዲህ ብሎ ጉዳዩን በዝርዝር ያብራራላቸው ጀመር፤ \v 5 እኔ በኢዮጴ ከተማ እጸልይ ነበር፤ በተመስጦም አራት ማዕዘን ያለው ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ መያዣ ከሰማይ ሲወርድ ራእይ ዐየሁ፤ ወደ እኔ ወረደ፣ \v 6 ትኵር ብዬ ተመለክትሁትና ስለ እርሱ ዐሰብሁ። አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳትን፣ አራዊትን፣ የሚሳቡ ፍጥረታትን፣ የሰማይ አዕዋፍንም ዐየሁ።