am_act_text_ulb/12/09.txt

1 line
526 B
Plaintext

\v 9 ጴጥሮስም መልአኩን ተከትሎ ወደ ውጭ ወጣ። መልአኩ ያደረገው ነገር በእውን እንደ ሆነ አላወቀም። ራእይ ያየ መሰለው። \v 10 የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ እንዳለፉ፣ ወደ ከተማይቱ ወደሚያወጣው የብረት በር ደረሱ፤ እርሱም ዐውቆ ተከፈተላቸው። እነርሱም ወጥተው በአንድ መንገድ በኩል ወረዱ፤ መልአኩም ወዲያውኑ ተለየው።