am_act_text_ulb/04/01.txt

1 line
665 B
Plaintext

\c 4 \v 1 \v 2 \v 3 \v 4 1 ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ፣ ካህናቱና የቤተ መቅደሱ ሹም፣ ሰዱቃውያንም ወደ እነርሱ መጡ። 2 ጴጥሮስና ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ሕዝቡን ያስተምሩና ከሙታን መነሣቱንም ያውጁ ስለ ነበረ እጅግ ተጨነቁ። 3 ያዟቸውና በዚያ ጊዜ ምሽት ስለ ነበረ እስከሚቀጥለው ጧት ድረስ በወኅኒ አቆዩአቸው። 4 ነገር ግን መልእክቱን ከሰሙት ብዙ ሰዎች አመኑ፤ ያመኑት ሰዎች ቍጥርም ዐምስት ሺሕ ያህል ነበረ።