am_act_text_ulb/02/08.txt

1 line
764 B
Plaintext

\v 8 \v 9 \v 10 \v 11 8 እያንዳንዱ በተወለድንበት ቋንቋ ሲናገር የምንሰማቸው ለምንድን ነው? 9 የጳርቴና፣ የሜድና የኢላሜጥ ሰዎች፣ በመስጴጦምያም፣ በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣ 10 በፍርግያም፣ በጵንፍልያም፣ በግብፅም፣ በቀሬና በኩል በሚገኙት የሊቢያ ክፍሎች የምንኖርም፣ ከሮም የመጣን፣ 11 አይሁድና ወደ ይሁዲነት የገባን ቀርጤሳውያንና ዐረባውያን የሆንን እኛ እነዚህ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎች በራሳችን ቋንቋዎች ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።