am_act_text_ulb/01/24.txt

1 line
564 B
Plaintext

\v 24 \v 25 \v 26 24 እንደዚህ ብለውም ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፣ የሰዎችን ሁሉ ልብ አንተ ታውቃለህ፤ ስለዚህ ከእነዚህ ከሁለቱ የትኛውን እንደመረጥኸው ግለጥ፤ 25 ይኸውም ይሁዳ ወደገዛ ስፍራው ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራ እንዲያገኝ ነው።” 26 ዕጣዎችን ለእነርሱ ጣሉ፤ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቆጠረ።