am_act_text_ulb/01/12.txt

1 line
773 B
Plaintext

\v 12 \v 13 \v 14 12 ከዚያም በኋላ የሰንበት ቀን ጉዞ ያህል ከሚያስሄደው፣ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ። 13 እዚያ ሲደርሱም ወደሚቆዩበት ወደ ላይኛው ሰገነት ወጡ። እነርሱም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ። 14 ሁሉም በአንድነት ሆነው ሴቶቹ፣ የኢየሱስ እናት ማርያምና ወንድሞቹም ጭምር በጸሎት ይተጉ ነበር።