am_act_text_ulb/01/09.txt

1 line
669 B
Plaintext

\v 9 \v 10 \v 11 9 ጌታ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ እነርሱ እየተመለከቱ ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረው። 10 ትኩር አድርገው ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ሳለ፣ ድንገት ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ። 11 “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።