am_act_text_ulb/28/13.txt

1 line
699 B
Plaintext

\v 13 ከዚያም ተጕዘን ወደ ሬጊዩም ከተማ ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላ የደቡብ ነፋስ ሽው አለ፤ በሁለት ቀንም ወደ ፑቲዮሉስ ከተማ መጣን። \v 14 እዚያም አንዳንድ ወንድሞችን አገኘንና ሰባት ቀን ከእነርሱ ጋር እንድንቆይ ተጋበዝን። በዚህ ዐይነት ወደ ሮም መጣን። \v 15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ከሰሙ በኋላ ሊቀበሉን እስከ አፒዮስ ገበያና እስከ ሦስቱ ማደሪያዎች ድረስ መጡ። ጳውሎስ ወንድሞች ባየ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመስግኖ ተጽናና።