am_act_text_ulb/25/23.txt

1 line
722 B
Plaintext

\v 23 ስለ ሆነም፣ በማግስቱ፣ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ከወታደራዊ መኮንኖችና ከከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ጋር ወደ አዳራሹ ገቡ። በፊስጦስ ትእዛዝም ጊዜ ጳውሎስን ወደ እነርሱ አመጡት። \v 24 ፊስጦስም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ እዚህ ከእኛ ጋር ያላችሁትም ሰዎች ሁሉ፣ ይህን ሰው ተመልከቱት፤ በኢየሩሳሌምና እዚህም ያሉት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ከእኔ ጋር ተማከሩ፤ ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወት መኖር የለበትም ብለውም ጮኹብኝ።