am_act_text_ulb/25/06.txt

1 line
644 B
Plaintext

\v 6 ፊስጦስም ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ከቆየ በኋላ፣ ወደ ቂሣርያ ወረደ። በማግስቱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ። \v 7 ጳውሎስም በደረሰ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ በአጠገቡ ቆሙ፤ በማስረጃ ማረጋገጥ ያልቻሉትን ብዙ ከባድ ክስም አቀረቡ። \v 8 ጳውሎስ፣ “በአይሁድ ስምም ላይ፣ በቤተ መቅደሱም ላይ፣ በቄሣርም ላይ በደል አልፈጸምሁም” ብሎ ራሱን ተከላከለ።