am_act_text_ulb/04/23.txt

3 lines
748 B
Plaintext

\v 23 ከተለቀቁ በኋላ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ራሳቸው ሰዎች መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው። \v 24 ሰዎቹ የነገሯቸውን ሲሰሙም፣ ድምፃቸውን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸው የሚገኘውንም ሁሉ የፈጠርህ ነህ፤ \v 25 በመንፈስ ቅዱስም በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦
‘አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ፣
ሕዝቡስ ከንቱ ነገርን ለምን ዐሰቡ?