am_act_text_ulb/23/09.txt

1 line
659 B
Plaintext

\v 9 በዚህ ጊዜ፣ ታላቅ ውካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍትም ተነሥተው፣ “ በዚህ ሰው ላይ አንድ ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነስ ማን ያውቃል?” በማለት ተከራከሩ። \v 10 ክርክሩም በጦፈ ጊዜ፣ ሻለቃው ጳውሎስን ይዘው እንዳይቦጫጨቁት ፈራ፤ ስለዚህ ወታደሮች ወርደው ጳውሎስን ነጥቀው ከሸንጎ አባላት መካከል ወሰደው ወደ ምዽጉ አምጥተው እንዲያስገቡት አዘዘ።