am_act_text_ulb/17/01.txt

1 line
431 B
Plaintext

\c 17 \v 1 አንፊጶል አጶሎንያ በተባሉ ከተሞች በኩል ካለፉ በኋላም፣ ተሰሎንቄ ወደ ተባለች ከተማ መጡ፤በዚያም ከተማ የአይሁድ ምኩራብ ነበረ። \v 2 ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ለሦስት ሰንበታት ያህል ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእርሱ ጋር ይነጋገር ነበር።