am_act_text_ulb/13/13.txt

1 line
712 B
Plaintext

\v 13 ጳውሎስና ጓድኞቹም በመርከብ ከጳፉ ተነሥተው በጵንፍልያ ወዳለችው ወደ ጴርጌን መጡ። ዮሐንስ ግን ትቶአቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። \v 14 ጳውሎስና ጓደኞቹ ከጴርጌን ተጕዘው የጲስድያ ወደ ሆነችው አንጾኪያ መጡ። በዚያ በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ። \v 15 ሕግና ነቢያት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እዚህ ላሉት ሕዝብ የሚሆን የሚያበረታታ መልእክት ካላችሁ፣ ተናገሩ” በማለት መልእክት ላኩላቸው።