am_act_text_ulb/22/14.txt

1 line
515 B
Plaintext

\v 14 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘ቅዱሱን እንድታይና ከገዛ አፉ የሚወጣውን ድምፅ እንድትሰማ፣ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ መርጦሃል፤ \v 15 ምክንያቱም ስለ አየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር ለሰዎች ሁሉ ምስክር ትሆንለታለህ። \v 16 ስለዚህ አሁን ለምን ታመነታለህ? ተነሥ፤ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅና ከኃጢአትህ ታጠብ።