am_act_text_ulb/21/39.txt

1 line
551 B
Plaintext

\v 39 ጳውሎስም፣ “እኔስ በኪልቅያ ከምትገኘው ከጠርሴስ ከተማ የመጣሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የታዋቂዋ ከተማ ዜጋ ነኝ። አንድ ነገር እለምንሃለሁ፤ ለሰዎቹ እንድናገር ፍቀድልኝ” አለው። \v 40 ሻለቃው በፈቀደለት ጊዜም፣ ጳውሎስ መወጣጫ ደረጃው ላይ ቆሞ፣ በእጁ ወደ ሕዝቡ አመለከተ። ሕዝቡ ጸጥ እረጭ ሲልም፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦