am_act_text_ulb/27/42.txt

1 line
679 B
Plaintext

\v 42 የወታደሮቹ ዕቅድ ከመካከላቸው ማንም ዋኝቶ እንዳያመልጥ እስረኞቹን ለመግደል ነበር። \v 43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ፈለገ፤ ስለዚህ ዕቅዳቸውን አልተቀበለም፤ መዋኘት የሚችሉትም በመጀመሪያ ከመርከቡ ላይ እየዘለሉ ወደ የብስ እንዲወጡ አዘዘ። \v 44 ከዚያም የቀሩት ሰዎች በሳንቃዎችና ከመርከቡ በተገኙ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው ተከትለው እንዲወጡ አደረገ። በዚህ ዐይነት ሁላችንም በደኅና ወደ የብስ ወጣን።