am_act_text_ulb/27/39.txt

1 line
838 B
Plaintext

\v 39 በነጋታውም፣ የነበሩበትን ምድር አላወቁትም፤ ነገር ግን በዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ መርከቡን ወደ ሰርጡ መግፋት ይችሉ እንደሆነም ተነጋገሩ። \v 40 ስለዚህ መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕሩ ላይ ተዉአቸው። በዚሁ ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈትተው ሸራውን ወደ ነፋሱ ከፍ አደረጉና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ። \v 41 ነገር ግን ሁለት ማዕበሎች ወደ ተገናኙበት ስፍራ መጡ፤ መርከቡም ወደ መሬት ገባ፤ የመርከቡ ቅስትም በዚያ ተተከለና የማይነቃነቅ ሆነ፤ የኋላ ክፍሉ ግን ከማዕበሉ ነውጥ የተነሣ ይሰባበር ጀመር።