am_act_text_ulb/27/27.txt

1 line
654 B
Plaintext

\v 27 በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት፣ በአድርያቲክ ባሕር ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን እያለን፣ እኩለ ሌሊት ገደማ፣ መርከበኞቹ ወደ መሬት የቀረቡ መሰላቸው። \v 28 የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ጣሉና ጥልቀቱን አርባ ሜትር ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ መለኪያውን ሲጥሉም ሠላሳ ሜትር ሆኖ አገኙት። \v 29 ከዐለቶቹ ጋር እንጋጫለን ብለውም ፈሩ፤ ስለዚህ ከኋላ አራት መልሕቆችን አውርደው ቶሎ እንዲነጋ ጸለዩ።