am_act_text_ulb/26/15.txt

2 lines
929 B
Plaintext

\v 15 እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' አልሁ። ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰልኝ፤ 'አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
\v 16 ተነሣና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥሁልህ አሁን ስለ እኔ ስለምታውቃቸውና ኋላ ላይ ስለማሳይህ ነገሮች አገልጋዬና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ነው፤ \v 17 ወደ እነርሱ ከምልክህ ሕዝብና ከአሕዛብም አድንሃለሁ ፤ \v 18 ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣን ኃይልም ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ ይኸውም በእኔ በማመናቸው ለራሴ የለየኋቸው እነርሱ፣ ከእግዚአብሔር የኃጢአትን ይቅርታና ርስትን እንዲቀበሉ ነው።'