am_act_text_ulb/21/22.txt

1 line
623 B
Plaintext

\v 22 እንግዲህ ምን እናድርግ? መምጣትህን እንደሚሰሙ ርግጠኞች ነን። \v 23 ስለዚህ አሁን እኛ የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች እዚህ አሉን። \v 24 እነዚህን ሰዎች ይዘህ ከእነርሱ ጋር ራስህን አንጻ፤ ጠጕራቸውን ለመላጨት የሚያስፈልጋቸውንም ገንዘብ ክፈልላቸው። በዚህም ስለ አንተ የተነገራቸው ሁሉ ውሸት እንደ ሆነ ያውቃሉ፤ አንተም ልማዱን ጠብቀህ እንደምትኖር ይረዳሉ።