am_act_text_ulb/21/07.txt

1 line
567 B
Plaintext

\v 7 ከጢሮስ የተነሣንበትን ጕዞ በጨረስን ጊዜ፣ አካ ደረስን። በዚያም ወንድሞችን አገኘንና አንድ ቀን ከእነርሱ ጋር ቈየን። \v 8 በሚቀጥለው ቀን ከዚያ ተነሥተን ወደ ቂሣርያ ሄድን። ከዚያም ከሰባቱ አንዱ ወደ ሆነው፣ ወደ ወንጌል ሰባኪው ወደ ፊልጶስ ቤት ገብተን ከእርሱ ጋር ሰነበትን። \v 9 ይህም ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።