\v 26 በምድር ገጽ ላይ የሚኖሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ የሚኖሩባቸውንም ስፍራዎች ወሰን፣ ወቅቶችንም የወሰነላቸው እርሱ ነው። \v 27 ስለዚህ እግዚአብሔርን ቢፈልጉ ሊያገኙት ይችላሉ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እርሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።