am_act_text_ulb/16/37.txt

1 line
727 B
Plaintext

\v 37 ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ሮማውያን የሆንነውን እኛን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበውናል፤ ወደ ወኅኒም አስገብተውናል፤ ታዲያ፣ አሁን በድብቅ ያስወጡናል? በፍጹም አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን።” \v 38 ጠባቂዎቹም ይህንኑ አባባል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ ገዦቹም ጳውሎስና ሲላስ ሮማውያን እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ። \v 39 መጥተውም ተማጸኑአቸው፤ ከወኅኒም ካስወጡአቸው በኋላ፣ ከከተማው እንዲወጡ ጳውሎስንና ሲላስን ለመኑአቸው።