am_act_text_ulb/16/01.txt

1 line
635 B
Plaintext

\c 16 \v 1 ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ መጣ፤ እነሆም፣ እናቱ አይሁዳዊት አማኝ የሆነች፣ አባቱ ግን ግሪክ የሆነ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር አገኘ። \v 2 በልስጥራና በኢቆንዮን የነበሩ ወንድሞችም ስለ እርሱ ጥሩ ምስክርነት ነበራቸው። \v 3 ጳውሎስም እርሱን ይዞ መጓዝ ፈለገ፤ በዚያ አካባቢ ስለ ነበሩ አይሁድ ሲልም ጢሞቴዎስን ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉም ያውቁ ነበርና።