am_act_text_ulb/15/24.txt

1 line
576 B
Plaintext

\v 24 እኛ ያላዘዝናቸው አንዳንድ ሰዎች ከእኛ ዘንድ መጥተው ነፍሳችሁን በሚያስጨንቅ ትምህርት እንዳስቸገሩአችሁ ሰምተናል። \v 25 ስለዚህ በአንድ ልብ ሆነን ሰዎችን መርጠን ከወዳጆቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ መላክ ለሁላችንም መልካም መስሎ ታየን፤ \v 26 እነዚህ ሰዎች ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲሉ ለሕይወታቸው እንኳ ያልሣሡ ናቸው።