am_act_text_ulb/15/07.txt

1 line
666 B
Plaintext

\v 7 ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ ቆመና እንዲህ አለ፦ «ወንድሞች ሆይ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከአፌ እንዲሰሙና እንዲያምኑ፣ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜያት በፊት ከእናንተ መካከል እኔን እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ።» \v 8 ልብን የሚያውቅ አምላክ፣ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ \v 9 በእኛና በእነርሱ መካከልም ልባቸውን በእምነት በማንጻት ልዩነት አላደረገም።