am_act_text_ulb/15/01.txt

1 line
561 B
Plaintext

\c 15 \v 1 አንዳንድ ሰዎች ከአይሁድ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ «በሙሴ ሥርዓት መሠረት ካልተገረዛችሁ መዳን አትችሉም» በማለት ወንድሞችን አስተማሯቸው። \v 2 ጳውሎስና በርናባስም ከእነርሱ ጋር ጥልና ክርክር በገጠሙ ጊዜ፣ ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲወጡ ወንድሞች ወሰኑ።