am_act_text_ulb/14/14.txt

1 line
854 B
Plaintext

\v 14 ነገር ግን ሐዋርያቱ፣ ባርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ልብሳቸውን ቀደው በመጮኽ፣ ፈጥነው ወደ ሕዝቡ መካከል ገቡ፤ \v 15 እንዲህም አሉ፤ «እናንተ ሰዎች፣ ለምን እነዚህን ነገሮች ታደርጋላችሁ? እኛኮ እንደ እናንተው ዐይነት ስሜት ያለን ሰዎች ነን፤ ወደ እናንተም የመጣነው ከእነዚህ ከንቱ ነገሮች፦ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ የምሥራች ቃል ይዘን ነው። \v 16 እግዚአብሔር ባለፉት ዘመናት አሕዛብን ሁሉ በገዛ መንገዳቸው እንዲሄዱ ተዋቸው።