am_act_text_ulb/14/08.txt

1 line
568 B
Plaintext

\v 8 በእግሩ መቆም የማይችልና ሽባ ከእናቱም ማሕፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። \v 9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ሰማ። ጳውሎስም ዐይኑን ተከትሎ ይህን ሰው ሲመለከት ለመዳን የሚያስችል እምነት እንዳለው አየ። \v 10 ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም” አለው፤ ሰውየውም ብድግ ብሎ ተነሣና ወዲያ ወዲህ ይመላለስ ጀመር።