am_act_text_ulb/09/38.txt

1 line
580 B
Plaintext

\v 38 ልዳ በኢዮጴ አጠገብ በመሆኑና ደቀ መዛሙርቱም የጴጥሮስን በዚያ መኖር ስለ ሰሙ፣ “ሳትዘገይ ወደ እኛ ና” ብለው በመለመን ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ። \v 39 ጴጥሮስም ተነሣና ከተላኩት ጋር ሄደ። እዚያ ሲደርስ፣ ወደ ሰገነቱ አወጡት። መበለታቱም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ትለብሳቸው የነበሩትን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩትና እያለቀሱ በአጠገቡ ቆሙ።