am_act_text_ulb/09/26.txt

1 line
567 B
Plaintext

\v 26 ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት ሞከረ፤ ነገር ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን በመጠራጠር ሁሉም ፈሩት። \v 27 ይሁን እንጂ፣ በርናባስ ወስዶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ አቀረበው። ሳውል ጌታን በመንገድ ላይ እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንደ ተናገረው፣ በኢየሱስ ስም ደማስቆ ውስጥ በድፍረት እንዴት እንደ ሰበከም ነገራቸው።