am_act_text_ulb/07/54.txt

1 line
592 B
Plaintext

\v 54 አሁን የሸንጎው አባላት እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ በልባቸው እጅግ ተቈጡ፣ ጥርሳቸውንም በእስጢፋኖስ ላይ አፋጩ። \v 55 እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣ ወደ ሰማይ አተኵሮ ተመለከተ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር አየ፤ ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየው። \v 56 እስጢፋኖስ፣ “እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየሁ” አለ።