am_act_text_ulb/07/44.txt

1 line
741 B
Plaintext

\v 44 አባቶቻችን የምስክሩ ድንኳን በምድረ በዳ ነበራቸው፤ ይኸውም ባየው ምሳሌ መሠረት መሥራት እንዳለበት እግዚአብሔር ሙሴን ሲያናግረው እንዳዘዘው ያለ ነው። \v 45 ይህ አባቶቻችን በተራቸው ከኢያሱ ጋር ወደ ምድሪቱ ያመጡት ድንኳን ነው። እግዚአብሔር በአባቶቻችን ፊት ባስወጣቸው አሕዛብ አገር ውስጥ ሲገቡ፣ ይህ ሆነ። እስከ ዳዊት ዘመን ድረስ እንደዚህ ነበር፤ \v 46 ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘ፤ ለያዕቆብ አምላክም ማደሪያ ስፍራን ለማግኘት ለመነ።